Telegram Group Search
አላህ ዘንድ እሺ የተባለ ዱዓ ሁሉ የቂን ነበር መጀመሪያው።… "አላህዬ ያደርገዋል" የሚል ፅኑ እምነት።

@fuadkheyr
@Fuadkheyr
የሆነ ሰዓት ትረጋጋለህ። ምንም ነገር እስከማይገርምህ ድረስ!!

@fuadkheyr
@fuadkheyr
መብቃቃት ከዚያም ፈገግ ማለት… ህይወት ከዚህ የበዛ ነገር አያስፈልጋትም።

@Fuadkheyr
@fuadkheyr
ከወደዱ…
(ፉአድ ኸይረዲን)

ጨረቃን ናፋቂ አይሸሽም ጨለማን
ብርሃን ፈላጊ፣
ትቀልጣለች ብሎ አይተዋትም ሻማን።

ወዳጅ የተባለ…ውበት ተመልክቶ፣
እሾሁን አይፈራም ፅጌሬዳን ሽቶ።

የተሸነፍክ እንደው
ለሀሳብ እምነቷ ለፀባይዋም ጭምር
ስለቁንጅናዋም ባድናቆትህ ዘምር

ምሉዕ ነገር …
በሰውኛ አዳራሽ
አይገኝም ጭራሽ!
@fuadkheyr
@fuadkheyr
ያለፉ አመቶች ካስተማሩህ ትምህርቶች መሀል "ሁለተኛ እድል አለመስጠት" ይገኝበታል ብዬ አስባለሁ።  የአንዳንድ ሰዎች እንቅስቃሴ ምንጫቸው ስህተት ሳይሆን ተፈጥሮዋዊ ቆሻሻነት ይሆናል። …  ቢደጋግሙት የማይሰለቻቸው  አማና ማጉደል፣ ክህደትና መሰል ክንውኖች።  እነዚህ ጋር ስትደርስ  "ከልክ ያለፈ ራስወዳድነትና ለጥፋቶቻቸው ውጤት ስሜትአልባ መሆናቸው" ምልክታቸው መሆኑን ማወቅ ይኖርብሃል። ሁለተኛ እድል በጭራሽ የማይታሰብላቸው!!

@fuadkheyr
@fuadkheyr
ድንገት ያለምንም ምክንያት… ከልክ በላይ ከምትወዳቸው ነገሮች ጀርባ መሮጥ ታቆማለህ። … የምትፈልገው ብቸኛ ነገር…  ሰላም መሆንና የልብ መረጋጋት ይሆናል።

@Fuadkheyr
@fuadkheyr
“አላህ  ባሪያው ለርሱ ብሎ የተሸከመውን ነገር ከንቱ አያደርግበትም።” 
ኢብኑል ቀይዪም
[ረውደቱል ሙሒቢን 460]

@Fuadkheyr
@fuadkheyr
አስቸጋሪ ቀናቶች እንዳልነበሩ ይጠቀለላሉ። እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች በስክነት ይለወጣሉ። ቁርአን ላይ የተጠቀሰው "የአዩብ የስቃይ ታሪክ ምናችን ነው?" … "የያዕቁብ ለቅሶ ምን ያደርግልናል?" … "ስለዩሱፍ የእንግልት ጉዞ ምናገባን?" … ይሄ ሁሉ መልዕክት አለው። “ከትዕግስት በኋላ ምቾት አለ" የሚል እና "ሁሉም ነገር ያልፋል" የሚል መልዕክት!!

@Fuadkheyr
@fuadkheyr
እዚያ ደግሞ ፍቅር ብለህ የምትጠራውን የምትሸሽ ጠንካራ ሴት ትመለከታለህ… ግን እርሷ ማፍቀርም መፈቀርም እንደሚገባት ውስጧ ያምናል… ምናልባት በየቂኗ ልክ አላህ የሚልክላትን አፍቃሪ የምትጠብቅ ናት… በበር በኩል… በበር!

ምናልባት ዓይኖቿ የሚናገሩት ካልገባህ ከአንደበቷ ብዙ ላታውቅ ትችላለህ… ዝምተኛ አይነት ትሆናለች…  ሰዎች ፊትለፊት ጀግና፣ መስታወቷ ፊት ግን ፈሪ ናት… "ድንጋይ" ነገር ናት ወይ? ብለህ እስክታስብ ድረስ ደረቅ መስላ ትታይሃለች… አህ የልቧን ልስላሴና ድክመት ስትሸፍነው አላየሀትማ…  በቃ… ፀሀይ በአንድ አይኗ ውስጥ ትኖራለች… ጨረቃ ደግሞ በሌላኛው ዓይኗ…

@Fuadkheyr
@fuadkheyr
“ወላሂ… ልብሱ  በመጠጥ ተነክሮ ባየውና ሽታው የማያስጠጋ ቢሆን እንኳን … ተደፍቶበት ነው እል ነበር…  ተራራ ላይ ቆሞ “አና ረቡኩም አልአዕላ” እያለ ሲጣራ ብመለከተው… የቁርአኗን አያ እያነበበ ነው ብዬ እላለለሁ…  ሂድ ከዚህ ሸምስን በዓይኔ አላየውም… በልቤ ነው የማውቀው”

ጀላሉዲን ሩሚ ነው ይህን ያለው… አንድ ሰው መጥቶ ስለ አስተማሪው ሸምስ አትተብሪዚ "ኸምር ሲጠጣ አይቼዋለሁ" ብሎ በማውራት በመሀከላቸው ቅራኔ ለመፍጠር ሲሞክር ሩሚ የመለሰለት ንግግር ነው።

ከልብህ ስለምታውቃቸው ሰዎች በጆሮህ አታብጠልጥላቸው… በሁሉም ነገር ላይ ከምታውቀው መሰረት የምትሰማውን አሉባልታ አታስቀድም… የምትሰማው ነገር የምታውቀውን እንዲጋርድብህም አትፍቀድ… በተለይ በእምነት ወንድሞችህ ላይ!!

@fuadkheyr
@fuadkheyr
የማለፍ ፀጋ የተሰጠው ሰው ትልቅ ስጦታ ተሰጥቶታል። ስህተቶችን ማለፍ፣ የተለዩ ስሜቶችን ማለፍ፣ ጥርጣሬዎችን ማለፍ።  በድርጊቶቻቸው ህይወትን ሊሰርቁብህ የሚፈልጉ ሰዎችንም ማለፍ መቻል ትልቅ የነፍስ ድል ነው።  ነገሮች ከታለፉ በኋላ ቀላል ይሆናሉ… ከትከሻህ ላይ ተራራ የተራገፈ እስኪመስልህ ድረስ መቅለል ይሰማሃል… ከማለፍ በኋላ።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
ከመሀከላችን ያልተቀየረው ማን ነው?…  ክስተቶች ይቀይሩናል፣ ከጓደኞቻችን ጋር መለያየት ይቀይረናል፣ ብቸኝነት ይቀይረናል፣ ሀላፊነት መሸከም ይቀይረናል፣ የድካም ጊዜዎቻችን ራሱ ይቀይሩናልኮ። ባደግን ቁጥር… ሃለታችንን፣ ዱንያንና ሰዎችን እየተረዳን እንመጣለን። በየጊዜው ቅድሚያ የምንሰጣቸው ጉዳዮች ይለዋወጣሉ። እንደነበረ የቆየ ማን አለ?…   መቀየራችንን ለጥሩ ያድርግልን እንጂ።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
እድሜሽ ስንት ነው?  ይጠይቋታል አንዳንዴ…  ልብ የሚከፍት ፈገግታዋን ትጥልና እንዲህ ትላለች “ህይወት የሰጠችኝን መንገድ ይዤ ስኖር የሀያ አመት ልጅ ነበርኩ። ቀናት በእናቴ ጎጆ ስር ሲያቀማጥሉኝ… የአመት ቁጥር እንኳን የማታውቅ ህፃን እሆናለሁ። በልቤ ውስጥ ፍቅር ሲቀሰቀስ  ደግሞ ምናልባት ስለፍቅር ዓለም ብዙ የምታውቅ  የሰላሳ አመት ሴት ሆኜ ራሴን አገኘዋለሁ። ህይወት ስታፈጥብኝና ፀሃይ አዘቅዝቃ ጨለማን ልታከናንበኝ ስትመጣ የሰማንያ አመት አዛውንት ልሆን እችላለሁ። ግን ሁሌ አበባ ነኝ።  የትኛውን እድሜ ነው የፈለጋችሁት?”

እንደሚባለው እድሜ ቁጥር ነው እያለች ይሆን?

@fuadkheyr
@fuadkheyr
“ምናልባት አንተ ተኝተህ ይሆናል… ላንተ የሚደረጉ በርካታ ዱዓዎች ግን የሰማይን በር ይቆረቁራሉ… ከረዳኸው ደሃ፣ ካበላኸው ራሀብተኛ፣ ካስደሰትከው ሀዘንተኛ፣ ፈገግ ካልክለት መንገደኛና ጉዳዩን ካቀለልክለት ችግርተኛ (የሚላኩ ዱዓዎች)… መቼም ቢሆን መልካም ስራን አቅልለህ አትመልከት።”
ኢብኑል ቀይዪም

@Fuadkheyr
@fuadkheyr
ውሃ እንኳን ዘግይቶ ሲመጣ  ድርቀት የገደለውን አበባ አያድነውም። ቆይተን ሁሉንም ይዘን ብንመጣ ራሱ…   በመዘግየታችን የምናጣቸው ነገሮች ይኖራሉ።  "ይዘገይ ይሆን ወይስ ልሂድ?" በማለት የሚጠብቁ ልቦችም እዚህ መሀል ይፈተናሉ። በመጨረሻም አላህ የወሰነው ይሆናል።

@Fuadkheyr
@fuadkheyr
በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ አንኳን ፍፁም ንፁህ "የይሆናል" ተስፋ ነበር። "ጌታዬ ጥሎ አይጥለኝም" የሚል  ፍፁም የቂንም ነበር። እኛ ዩኑስን አይደለንም። የዩኑስ አይነት ተስፋ አስቆራጭ ሃለት ውስጥም አልገባንም። ግን በትንሽ ፈተና ተስፋ እንቆርጣለን። "በጨለማዎች ውስጥም ተጣራ።” [ዩኑስ]

@fuadkheyr
@fuadkheyr
ፍቅር ያረጃል፣ ጓደኝነትም ይደበዝዛል… በምን? በቸልተኝነት!

@fuadkheyr
@fuadkheyr
ከእጅህ በፊት በፈገግታህ  ሰላም በለኝ።  ያኔ ከእጄ በፊት ልቤን አግኝተህ እንደምትጨብጠው እርግጠኛ ሁን። ራሃ እሆንልሃለሁ። ነብይህ "በወንድምህ ፊት ላይ ፈገግ ማለት ሰደቃ ነው" ማለታቸውንም አትርሳ።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
ከጊዜ ጋር የጭቅጭቅ ምክንያቶችንም ትረሳቸዋለህ። ሁሉም መጥፎ የነበሩ ዝርዝር ጉዳዮችህ ከሀሳብህ ይተናሉ። ዘወትር የማይፋታህ አንድ ጥያቄም ይኖራል… “የተፈጠረው ነገር ሁሉ  ተገቢ ነበር ወይ?” … በስራ ጉዳይ፣ በጓደኝነትና በቤተሰብ ሁኔታ ለሚያጋጥሙ ጉዳዮች…

@fuadkheyr
@fuadkheyr
“እፈልግሀለሁ”  ይህ ቃል ለአድማጩ ቀላል፣ ለተናጋሪው ደግሞ እጅግ ከባድ የሆነ ቃል ነው። ምናልባት ተናጋሪው የሚያሳፍረውና የሚያሳምመው ጉዳይ መሀል  ላይ የሚወጣ ቃል ነው።  ደካማነቱን ለመሸፈን የሚጥርበት ሌላ ዘዴም ይሆናል አንዳንዴ።  በዚህ ቃል የሚያናግሩን ሰዎች ትኩረት መስጠት ይኖርብናል።  ከጉዳያቸው መሀል እነርሱን ማንጠልጠል በደል ስለሚሆንብን።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
2024/06/29 10:03:23
Back to Top
HTML Embed Code: